
የተቀናጀ የምንነት ምልክትዎን አጽንተው በሚያስዉቡ እና አሳታፊ የተጠቃሚ ተሞክሮን ለሁሉም ተጠቃሚዎችዎ በመስጠት እና ለእይታ ማራኪ በይነገጾችን በማሳመር እሰራልዎታለሁ።

የተጠቃሚዎችዎን ፍላጎቶችና ባህሪ አጥንተን ምክኒያታዊ ፍሰትን እና እንከን የለሽ መስተጋብርን በአስተማማኝነት እሰራልዎታለሁ።

ግልጸኝነትን እና ትኩረትን ለማረጋገጥ የዲጂታል ምርትዎች መዋቅራዊ አቀማመጥ ከዋናው ንድፍ ቀድመን አሳይዎታለሁ።

የርስዎን ግብረ መልስ ወይንም አስተያየት ለመስማት፣ የተነደፈው ንድፍ እንደፍላጎትዎ እንደሆነ የንድፍ ውሳኔዎችን ለማረጋገጥ፡ የሙከራ ንድፎችን ወደ መስተጋብራዊ ማሳያ ለውጠን አሳይዎታለሁ።

የንድፉን አስቸጋሪ ቦታዎች ለመለየት እና አጠቃላይ የተጠቃሚን ተሞክሮ ለማመቻቸት ምርትዎትን ተጠቃሚ ሊሆኑ ከሚችሉ ትክክለኛ ሰዎች ላይ እያየን ንድፍዎትን እናሻሽልልዎታለን።
አዳዲስ ቪዲዮዎቼ ሲለቀቁ ቶሎ እንዲደርስዎ @habtedotcoን መከተልዎን አይርሱ።