የምሰጣቸው አገልግሎቶች

የድር መተግበሪያ፣ የሞባይል መተግበሪያ፣ UI/UX ዲዛይን እና በሌሎችም መስኮች የምሰጣቸውን አገልግሎቶች ያስሱ።

ነፃ ምክክር

ደውሉልኝ ፡ ከዛም ምን እንደሚጠቅምዎት እና እንዳማይጠቅምዎት እወያያለሁ። በውይይታችን ላይ ምን ቢወስኑ እንደሚያዋጣዎት እና የእርስዎን ጥያቄዎች ብቻ እንመልሳለን እንጂ አገልግሎቶቼን ለመሸጥ ለማሳመን አልሞክርም። የ20 ደቂቃ ብቻ ውይይት።

ላግዘዎት የምንችላቸው ነገሮች

የምርትዎን እምቅ ሃይል በገሃድ አሳይልዎታለሁ!

የዲዛይን አጋርነት

የዲዛይን ውቅርዎትን ዘመናዊነቱን እንዲጠብቅ ለማድረግ እና ለማደስ።

የምርትዎን ራዕይ የተሳካለት እናደርግልዎት

ዘመናዊ የዲዛይን ዘይቤና አዳዲስ የዲዛይን አይነቶችን በመከተል ተዛማጅ የዲዛይን ስርዓት ከእኔ ጋር በመስራት ያግኙ። ይህም የምርትዎ ስራዎች ዘመናዊነታቸውን እንዲጠብቁ እና ከተወዳጅ ደንበኞችዎ ጋር ይበልጡን እንዲቀራረቡ ያደርጋል።

አንድ ላይ፡ የስራዎችዎን እያታ ማራኪ እና ሳቢ አደርግልዎታለሁ። ይህም በኢንድስትሪዎ ፈር ቀዳጅ እና የገበያ ህያውነትዎንም እንዲጠበቅ ያደርግዎታል።

ያግኙኝ

ዲዛይን ማሻሻል

አዲስ እና ዘመኑን የዋጀ እንዲሆን ለሚያስፈልጋቸው ድረ-ገጾች

ድረ-ገጽዎን ያዘምኑ

ድረ-ገጽዎ ያረጀና የማያምር መስሎ ከተሰማዎት፡ የዲዛይን ማሻሻል አገልግሎታችን አዲስ እና ዉብ የተጠቃሚ ተሞክሮ በዘመናዊ UI/UX ምርጥ ልምዶች አስተካክልልዎታለሁ። ይህም ሊያስተላልፉት የፈለጉትን መልእክት በሚስብ እና በሚያምር መልኩ እንዲቀርብልዎት ያደርጋል።

የድረ-ገጽዎን ውበት እና የተጠቃሚ ተሞክሮን እንዲጠብቅልዎ፣ የተሻለ የተጠቃሚ ተሞክሮን እና ምርጥ የተባሉ ልምዶችን በመጠቀም የድረ-ገጽዎን መልኩን እና የተጠቃሚነት ቅለቱን እንዲጠብቅ ላድርግልዎ

የተዋበ ዲዛይን ያግኙ

ነገሮችን ለማመቻቸት

ያዘገመ እና ቀርፋፋ አሰራር ላላቸው ዌብሳይቶች

የምንራቀቅለት የመተግበሪያዎች ፍጥነት

ድረ-ገጽዎ ዝግታውና መንቀራፈፉ ደንበኞችን ሊያሳጣዎትና መልእክትዎት ቶሎ ተደራሽ ላይሆን ይችላል። ይህንን የመቅረፍ አቅም አለኝ፣ እነሱም ድረ-ገጽዎ በፍጥነት እንዲከፍትና በፍጥነት እንዲሰራ በማድረግ ደንበኞቻችሁ እንዲቆዩ እና የፈለጉትን መረጃ እንዲያገኙ አደርግልዎታለሁ።

Googleና የመሳሰሉት ላይ ቶሎ ተፈልገው እንዲገኙ እናደርግዎታለን። ይህም ተጠቃሚዎችዎን የሚያረካና የፈለጉትን ምርት በተቀላጠፈ ሁኔታ ለማቅረብ ይረዳዎታል።

አሁኑኑ ያቀላጥፉ

የAI ውህድ

AI ለተሳለጡ አፈጻጸሞች።

ወደ ወደፊት ይጓዙ

የAI ኃይልን ለመጠቀም ዝግጁ ነዎት? ChatGPT, Claude, DeepSeek, Gemini ወይም የሚመረጡትን AI ሞዴል በዲጂታል መድረኮችዎ ላይ ለተሳለጡ አፈጻጸሞች ላዋህድልዎ።

ከውድድሩ ቀድመው ለመቆም እና ለተጠቃሚዎች ጥሩ ተሞክሮዎችን ለማቅረብ በሰው ሰራሽ አስተውሎትን ይጠቀሙ።

AIን አዋህድልኝ

በጣም ፈጣን ድረ-ገጽ

በጣም ፈጣን እና ቀልጣፋ የሆነ ድረ-ገጽ እንዲኖችዎት።

በጣም ፍጥነት ያለዉን ድረ-ገጽ አስጀምሩ

የሚያምር ዲዛይንን ከላቀ አፈጻጸምና ፍጥነት ጋር በመዋሃድ ዘመናዊ የሆነ የድረ-ገጽ ተሞክሮ እንገንባልዎ። በምንገነባልዎ ሂደት ፈጣን እና ሳቢ የሆነ፡ የተጠቃሚን ፍላጉት በቀላሉ እንደሚያከናውኑ አረጋግጥልዎታለሁ።

የምርትዎን ዕድገት እና የምርት ፍላጎቶችዎን በሚስብ እና በሚያምር መልኩ መልእክትዎትን ለደንበኛዎት ያስተላልፉና ተወዳዳሪዎችዎን ይብለጡ።

አሁኑን ይገንባልኝ
ከዚህ በታች ያሉት የብራንዲንግ እና የግራፊክስ አገልግሎቶች የሚሰጡት አብሬያቸው በምሰራቸው የተካኑ ዲዛይነሮች በኩል ነው

የማንነት ምልክት(Branding) ማሻሻል

የምንነት ምልክትዎ (Branding) ዋና ትልሙን እንዲገልጽ እና አዲስ መንፈስ እንዲኖረው።

የማንነት ምልክትዎን(Branding) ያሻሽሉ

የማንነት ምልክት(Branding) ማሻሻል አገልግሎታችን ውብ ያልሆነ የምርት ምልክቶችን እና እይታዎችን አዲስ መንፈስና መልክ በመስጠት ከተወዳዳሪዎች በላይ እንዲሆኑ እናም ከገበያው ተሽለው እንዲገኙ ያደርግዎታል።

የምርትዎን ምልክት እንደገና ለመገለጽ፣ ደንበኞችዎን ለመማረክ እና የምርትዎን ምልክት(Branding) ለማሻሻል ይፍቀዱልኝ።

አሁኑኑ አሻሽሉልኝ

የሎጎ ዲዛይን እና ሪዲዛይን

ሎጎዎ በትክክል ይሰራል - ከዛ በላይም ከዛ በታችም አይደለም

መለያዎን ይፍጠሩ

ልዩ፣ ዘመን ተሻጋሪ እና ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ ሎጎዎችን ከሚሰሩ የተካኑ የብራንድ ዲዛይነሮች ጋር በጋራ እሰራለሁ። በዘመኑ ፋሽን ብቻ ሳይሆን አላማን መሰረት ያደረጉ ናቸው። እያንዳንዱ የሚሰሩት ሎጎ ከተሟላ የብራንድ መለያ ስርዓት ጋር ይመጣል፦ የቀለም ምርጫ፣ የፊደል አጠቃቀም፣ የአጠቃቀም ህጎች እና የብራንድ መመሪያዎች። ይህም ብራንድዎ በሁሉም ቦታ ላይ በግልጽ እንዲታወቅ ያደርገዋል።

ይህ ማለት ከሎጎ ብቻ በላይ ያገኛሉ ማለት ነው። የተሟላ መሰረት ያገኛሉ፦ የቀለም ስርዓት፣ የፊደል ተዋረድ፣ የብራንድ ድምጽ መመሪያዎች፣ ማድረግ ያለብዎት እና የሌለብዎት የአጠቃቀም ህጎች፣ እና ኩባንያዎ ወጥነት እና ተአማኒነት እንዲኖረው የሚያስፈልገውን ሁሉ ያገኛሉ።

የማንነት ምልክት(Branding)

ጎልቶ የሚወጣ እና ህልውናውን የሚያስተጋባ የምንነት ምልክት

ስለ ምንነት ምልክትዎን መግለጫ አስቡ

የሚያስተጋባ የምንነት ምልክት እንዲኖረዎት ይፈልጋሉ? መልካም። ታሪክዎትን ሳቢ እና ዉብ በሆኑ ምስሎች መልእክትዎትን ያንዣበበ አድርጌ እሰራልዎታለሁ።

የምርትዎን ምልክት እናሸብርቅልዎ

የግራፊክስ ዲዛይን አውታረ መረብ

ሰፋ ያለ የግራፊክስ ስራ ይፈልጋሉ? ባለሙያዎችን አውቃለሁ

ከምርጦቹ ጋር የተገናኘ

ስራዬ የሚያተኩረው በዲዛይን እና ኢንጂነሪንግ ውህደት ላይ ነው። ነገር ግን ፕሮጀክትዎ ሰፋ ያለ ግራፊክስ፣ ስዕላዊ መግለጫዎች ወይም ጠለቅ ያለ የእይታ ይዘት የሚጠይቅ ከሆነ፣ አብሬያቸው የምሰራቸው እና የማስተዋውቅዎ የተካኑ የግራፊክስ ዲዛይነሮች አውታረ መረብ አለኝ።

የሶፍትዌር ፕሮጀክቶች ሲጠይቁም፣ የተጠቃሚውን ተሞክሮ (UI/UX) ይበልጥ ማራኪ ለማድረግ ከግራፊክስ ዲዛይነሮች ጋር በንቃት እሰራለሁ። ምርጥ ስራዎች በሁሉም ደረጃ ምርጥ እይታ ይገባቸዋል።

ስለ ፕሮጀክትዎ ይንገሩኝ

habte.co — የቅርብ ስራየን

ፕሮጀክቶች

የሚታሰብዎት ፕሮጀክት አለ? አብረን አዲስ ነገር እንፍጠር

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ — በዓለም ዙሪያ የሚገኝ

ተደጋግመው የሚጠየቁ ጥያቄዎች

ስለአገልግሎቶቼ እና ሂደቶቸ ለሚነሱ የተለመዱ ጥያቄዎች መልሶችን ያግኙ።

የተጠቃሚ በይነገጽ እና ተሞክሮ ዲዛይን(UI/UX) እና የድረ ገጽ አገልግሎቶችን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቼ እሰራለሁ። ለተለዩ ፍላጎቶችዎ የተዘጋጁ አጠቃላይ የዲጂታል መፍትሄዎችን ለመፍጠር ቁርጠኛ ነኝ። ዝርዝር መረጃ ለማግኘት እባክዎ የአገልግሎቶቼን ገጽ ይጎብኙ።

ከእኔ ጋር ለመስራት ፍላጎቱ አለዎት?